Washington State

Office of the Attorney General

Attorney General

Bob Ferguson

የእርግዝና እና የጡት ማጥባት እገዛዎች


የእርግዝና እና የጡት ማጥባት እገዛዎች

የዋሽንግተን ሕግ ለነፍሰ ጡር ሠራተኞች የተወሰኑ የሲቪል መብቶች ጥበቃዎችን ይሰጣል። እነዚህ ጥበቃዎች ለሠራተኛዋ እርግዝና እና ከእርግዝና ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና ሁኔታዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፤ ይህም የጡት ማጥባት ወይም ወተት የመስጠት ፍላጎትን የመሳሰሉ በእርግዝና ወቅት እና ህፃኑ ከተወለደ በኋላ ያሉ የጤና ሁኔታዎችን ያጠቃልላል። ነፍሰ ጡር ሠራተኛዋ ከ 15 ሠራተኞች ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ አሠሪ የምትሠራ ከሆነ፣ አሠሪው የሚከተሉትን ምክንያታዊ እገዛዎች ለሠራተኛዋ እንዲያቀርብ ይጠየቃ፦የነፍሰ ጡር ሠራተኞች የእገዛ መብቶች

1. ረጅም፣ ተደጋጋሚ ወይም ተለዋዋጭ የመጸዳጃ ቤት እረፍቶችን መስጠት፤

2. የምግብ እና የመጠጥ ክልከላ ፖሊሲን ማስተካከል፤

3. መቀመጫ መስጠት ወይም ሰራተኛዋ ብዙ ጊዜ እንድትቀመጥ መፍቀድ፤ እና

4. ከ 17 ፓውንድ በላይ ከማንሳት መታቀብ።

በተጨማሪም፣ ለአሠሪው ከፍተኛ ችግር ወይም ወጭ እስከሌለ ድረስ፣ ነፍሰ ጡር ሠራተኛዋ ለሌሎች የሥራ ቦታ እገዛ(ዎች) መብቶች ሊኖራት ይችላል። እነዚህም፦

5. የሥራ መርሃ ግብር መቀየር፣ ሥራን እንደገና መመደብ፣ የሥራ ጣቢያ መቀየር ወይም አንዳንድ መገልገያዎችን መስጠትን ጨምሮ የሥራ መርሃግብርን እንደገና ማዋቀር፤

6. ወደ ቀላል ወይም አነስተኛ አደጋ ሊፈጠር ወደሚችልበት ቦታ ጊዜያዊ ሽግግር ማድረግ፤

7. ለቅድመ ወሊድ ጉብኝቶች ተለዋዋጭ የጊዜ ሰሌዳ ማውጣት፤

8. ሰራተኛዋ ህፃኑ ከተወለደ በኋላ የጡት ወተት ለሁለት አመት ያህል እንዲወስድ ተመጣጣኝ የእረፍት ጊዜ በመስጠት ሰራተኛዋ ወተቱን ማውጣት ባስፈለጋት ጊዜ ከመታጠቢያ ቤት ውጭ የግል ቦታን ማቅረብ፤ እንደዚህ ያለ ቦታ በስራ ቦታ ካለ፣ ሰራተኛዋ ወተት ለማውጣት ሊያገለግላት ይችላል። የንግድ ቦታው ሰራተኛዋ ወተት የምታወጣበት ቦታ ከሌለው፣ አሠሪው ፍላጎቷን ለማመቻቸት ምቹ ቦታና የሥራ መርሃ ግብር ለመለየት ከሠራተኛዋ ጋር አብሮ መሥራት አለበት፤ እና

9. ሰራተኛዋ ሊያስፈልጋት የሚችለውን ማንኛውንም ተጨማሪ እገዛ ማቅረብ።

አሠሪዎች ከላይ ከ 1-4 ባለው ውስጥ ለሚገኙ እገዛዎች ከጤና ባለሙያ የጽሑፍ ማረጋገጫ ሊጠይቁ አይችሉም። ከዚህ በላይ ባሉት ከ 5–9 ያሉትን እገዛዎች አስፈላጊነት፣ ወይም 17 ፓውንድ ወይም ከዚያ በታች ለማንሳት ገደቦችን በተመለከተ አሠሪዎች የጽሑፍ ማረጋገጫ ከጤና እንክብካቤ ባለሙያ ሊጠይቁ ይችላሉ።

አሠሪዎች ከእነዚህ ለውጦች ውስጥ አንዱን በሚጠይቁ ነፍሰ ጡር ሠራተኞች ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ፣ ሌላ ብቃት ላላቸው ነፍሰ ጡር ሠራተኞች የሥራ ዕድል እንዳያገኙ ማድረግ፣ ወይም ደግሞ ድርጅቱ አማራጭ ሲያገኝ ነፍሰጡሮቹን የግድ ዕረፍት እንዲያደርጉ ማድረግ የተከለከሉ ናቸው። በተጨማሪም ከእርግዝና ጋር የተዛመደ የአካል ጉዳተኛ ነፍሰ ጡር ሠራተኞች እዚህ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ መብቶች ሊኖራቸው ይችላል። የ Civil Rights Division (የሲቪል መብቶች ክፍል) አንድ አሠሪ የሠራተኛን እርግዝና ማገዝ አልቻለም የሚሉ ቅሬታዎችን ይቀበላል። pregnancy@atg.wa.gov ላይ ወይም በነፃ ስልክ መስመራችን (833) 660-4877 ላይ መልእክት በመተው ሊያነጋግሩን ይችላሉ። የእኛን የኦንላይን ቅፅ በመጠቀም ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ እንዲሁም የሰራተኛ አባል የእርስዎን ጉዳይ ይከተላል።


ለአሰሪ እና ሰራተኛ የእርግዝና እገዛ መመሪያ

ይህ ባለ አንድ ገጽ በራሪ ወረቀት በዋሽንግተን ግዛት ሕግ መሠረት ለነፍሰ ጡር ሠራተኞች ስለሚያስፈልጉት ልዩ እገዛዎች መረጃ ይሰጣል። በራሪ ወረቀቱ ሠራተኞችንም ሆነ አሠሪዎችን በሕጉ መሠረት ያላቸውን መብትና ግዴታ ለማሳወቅ የተዘጋጀ ሲሆን በእንግሊዝኛም ሆነ በስፓኒሽ ይገኛል።

በራሪ ወረቀቱ የእርግዝና እገዛ ሕጎች ምን እንደሆኑ፣ ነፍሰ ጡር ሠራተኞች በሥራ ቦታ ያላቸውን መብቶች፣ ለአሠሪዎች የተከለከሉ ልምዶችን እና ነፍሰጡር ሠራተኞች የእርግዝና እገዛ ጥሰቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ ይዘረዝራል።