ኦገስት 12፣ 2025
SEATTLE —ዋሽንግተን የጥላቻ ወንጀሎችን እና የመድሎ ክስተቶች የቀጥታ መስመር ሙከራ በግዛቱ ውስጥ ባሉ ሶስት ካውንቲዎች ጀምራለች። በFederal Bureau of Investigation (FBI፣ የፌዴራል የምርመራ ቢሮ) የጥላቻ ወንጀሎች ስታቲስቲክስ መሰረት ዋሽንግተን ከ2018 ጀምሮ አብዛኞቹ የጥላቻ ወንጀል ሪፖርቶች ሪፖርት ከተደረጉባቸው አምስት ዋና ግዛቶች መካከል አንዷ ነች። የድንገተኛ ጊዜ ያልሆነ የስልክ መስመር በክላርክ፣ ኪንግ እና ስፖካን ካውንቲዎች ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የጥላቻ ወንጀሎችን ወይም የመድሎ ክስተቶችን ሪፖርት ለማድረግ አማራጭ መንገድ ያቀርባል።
የጥላቻ ወንጀሎች እና የመድሎ ክስተቶች በግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ላይ የሚያጠፋ እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሲሆን ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ የማይፈለጉ ወይም ደህንነታቸው ያልተጠበቀ እንደሆነ እንዲሰማቸው ያደርጋሉ። የስልክ መስመር ሰራተኞች የሚደውሉ ሰዎች በአካባቢው የሚገኝ፣ በባህል ደረጃ ብቁ የሆነ፣ ተጎጂዎችን ያማከለ እና የአሰቃቂ አጋጣሚ የድጋፍ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያግዛሉ እንዲሁም በሚደውለው ሰው ፈቃድ ክስተቶችን ለአካባቢው ህግ አስከባሪ ሪፖርት በማድረግ ይረዳሉ።
የስልክ መስመሩ ወደ 1-855-225-1010 በመደወል ይገኛል። እንዲሁም በሶስቱ የሙከራ ካውንቲዎች ውስጥ የጥላቻ ወንጀል ወይም የመድሎ ክስተት ሪፖርት ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው atg.wa.gov/report-hate መጎብኘት ይችላል።
የLegislature (የሕግ አውጭው) በሁለት ወገኖች ድጋፍ የ Senate Bill 5427 ን (ሴኔት ቢል 5427 ን) ሲያጸድቅ በ2024 የቀጥታ ስልክ መስመሩን ፈጥሯል። የህግ ረቂቁ በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ በሶስት ካውንቲዎች ውስጥ ለሚገኘው የስልክ መስመር በAttorney General’s Office (በጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት) የሚተዳደር የሙከራ ፕሮግራም ያስፈልገዋል - በምስራቅ ዋሽንግተን የሚገኘውን ጨምሮ። ሶስቱ ካውንቲዎች በ2023 Washington Association of Sheriffs and Police Chiefs Annual Crime Report (አመታዊ የወንጀል ሪፖርት) እና የካውንቲዎች የስነ ህዝብ አወቃቀር ላይ በሚገኙት የጥላቻ ወንጀሎች ውሂብ ላይ በመምስረት ተመርጠዋል።
የሙከራ ፕሮግራሙ ለአንድ አመት ተኩል የሚሰራ ይሆናል ከዚያ የስልክ መስመሩ በጃንዋሪ 2027 በግዛት አቀፍ ደረጃ የሚጀመር ይሆናል። የጥላቻ ወንጀሎች እና የመድሎ ክስተቶች በበቂ ሁኔታ ሪፖርት አልተደረጉም እና ስርጭታቸውን የተመለከተው መረጃ የተገደበ ነው። ከጁላይ 1፣ 2027 ጀምሮ Attorney General’s Office ከቀጥታ ስልክ መስመር ሪፖርቶች የተሰበሰበውን መረጃ የሚገልጽ የጥላቻ ወንጀሎችን እና የመድሎ ክስተቶችን በተመለከተ ለገዥው፣ ለግዛት ለLegislature እና ለህዝብ ዓመታዊ ሪፖርት ያዘጋጃል።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ Nick Brown “የጥላቻ ወንጀሎች ግለሰቦችን በቀጥታ መጉዳት ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ ውስጥ ላይ ጉዳትን ሊጨምሩ ይችላሉ” በማለት ተናግረዋል። “በእነዚህ ሶስት ካውንቲዎች ውስጥ የሚኖረው ስኬት የስልክ መስመሩን በግዛት አቀፍ ደረጃ ለማስፋት እና በዋሽንግተን ያሉ የጥላቻ ወንጀሎችን እና የመድሎ ክስተቶችን እንዴት መዋጋት እንደምንችል በተሻለ እንድንረዳ ይረዳናል።”
የአማካሪ ቡድኑ አባላት እና የአካባቢው ባለስልጣናት የቀጥታ መስመር ሙከራው መጀመሩን በተመለከተ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል፦
“የጥላቻ ወንጀል ህጎቻችንን በመቀየር በ2019 አንድ አስፈላጊ እርምጃ ወስደናል - ነገር ግን የጥላቻ እና የመድሎ ክስተቶች መጨመር አሁንም ብዙ መስራት እንዳለብን ያሳያል” ሲሉ የስልክ መስመሩን የፈጠረውን ህግ አውጪ ስፖንሰር ያደረጉት Sen. Javier Valdez, D-Seattle ተናግረዋል። “ይህ የስልክ መስመር የሚያስፈልገው ለዚያ ነው። ስለ ፖሊሲ ብቻ አይደለም - ስለ ሰዎች ነው። እያንዳንዱ ተጠቂ መሰማቱን እና ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግን የሚመለከት ነው።”
“ጥላቻ ያለው የፌደራል አስተዳደር በተጋላጭ ማህበረሰቦች ላይ አክራሪነትን በሚያባብስበት ወቅት፣ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ብዙዎች በፍርሃት እና በጥርጣሬ እየኖሩ ነው” በማለት የኪንግ ካውንቲ ምክር ቤት ሊቀመንበር Girmay Zahilay ተናግረዋል። “በዚህ ተነሳሽነት Attorney General’s Office በመቀላቀሌ ኩራት ይሰማኛል እንዲሁም ለዚህ ጅምር አስተዋዕዖ ላበረከቱ የማህበረሰብ መሪዎችን አመሰግናለሁ። አንድ ላይ ጥላቻን በመቃወም አንድነታችንን እንቀጥላለን።”
“Spokane አዲሱን Hate Crimes & Bias Incidents Hotline (የጥላቻ ወንጀሎች እና አድልዎ ክስተቶች ሆትላይን) መጀመር በደስታ የሚቀበል ሲሆን ከሶስቱ የመጀመሪያዎቹ የሙከራ ቦታዎች አንዱ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል” በማለት የስፖካን ከንቲባ Lisa Brown ተናግረዋል። “የእኛ Office of Civil Rights, Equity, and Inclusion (የሲቪል መብቶች፣ ፍትሃዊነት እና አካታች ቢሮ) ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን ጋር በልማቱ ላይ ተሰማርቷል እንዲሁም ሪፖርት ማድረግን ለማሻሻል እና በማህበረሰባችን ውስጥ ተተያቂነትን ለማረጋገጥ ይህንን እንደ ወሳኝ መሳሪያ እንመለከታለን።”
“የስፖካን ካውንቲ የHate Crimes Hotline ፕሮግራም በመሞከር እየመራ በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል” በማለት የስፖካን ካውንቲ ኮሚሽነር Amber Waldref ተናግረዋል። “ይህ መሳሪያ በማህበረሰባችንን ውስጥ ያለውን ሰው ደህንነት እና ጥበቃ ለማረጋገጥ ነዋሪዎች ሊሆኑ የሚችሉ የጥላቻ ወንጀሎችን ሪፖርት እንዲያደርጉ አዲስ እድል እንደሚፈጥር ተስፋ አደርጋለሁ።”
“ይህ የስልክ መስመር ሰዎች የጥላቻ ወንጀሎችን ሪፖርት ለማድረግ ደህንነት እንዲሰማቸው ለማድረግ ጠቃሚ እርምጃ ነው” በማለት የክላርክ ካውንቲ የፖሊስ መኮንን John Horch ተናግረዋል። “በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ድምጻቸው ጠቃሚ እንደሆነ እና እርዳታ እንዳለ እንዲያውቁ እንፈልጋለን።”
“የእስያ፣ የሃዋይ ተወላጅ እና የፓሲፊክ ደሴት ማህበረሰብ የጥላቻ ወንጀሎች እና የመድሎ ክስተቶች ለመቶ አመታት ያጋጠመው ሲሆን ወረርሺኙ በጨመረበት ወቅት ጎልቷል” በማለት የHAPPEN Business Resource Group የጋራ ሊቀመንበር፣ Thanh Tran ተናግረዋል። “እነዚህ ክስተቶች በየቀኑ መከሰታቸው የቀጠለ ሲሆን በዋና ዋና የዜና ማሰራጫዎች ውስጥ በትንሹ ወይም ምንም አልተጠቀሰም። ማህበረሰቡን ማብቃት እና ወደ ፍትህ እና ፈውስ እንድንሄድ ይህ የስልክ መስመር ተጎጂዎች እነዚህን ክስተቶች ሪፖርት እንዲያደርጉ እንደሚያበረታታ ተስፋ አደርጋለሁ።”
“የስልክ መስመሩ ማህበረሰቦቻችን ሁል ጊዜ የሚያውቁትን ነገር ስለሚያረጋግጥ በጣም አስፈላጊ ነው፦ ጥላቻ የአካል ጉዳት ወይም የንብረት ውድመት በሚጠይቁ ጠባብ የህግ ፍቺዎች ውስጥ ብቻ አይኖርም” በማለት የWashington Immigrant Solidarity Network ዋና ዳይሬክተር፣ Catalina Velasquez ተናግረዋል። በእኔ አውታረ መረብ ውስጥ ያሉ ስደተኛ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ እንዲፈሩ የሚያደርጋቸው የቃላት ትንኮሳ ሲያጋጥማቸው፣ ጾታቸውን የቀየሩ ጥቁር ሰዎች በየቀኑ ሰብዓዊነታቸውን ቀስ በቀስ የሚቀንሱ ጥቃቅን ጥቃቶች ሲያጋጥሟቸው፣ አረጋውያን ‘ወደመጡበት ቦታ ተመለሱ’ ሲባሉ — እነዚህ የእኛን ቁሳዊ ሁኔታዎች እና በአለም ላይ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የመኖር ችሎታችንን የሚቀርጹ የጥቃት ድርጊቶች ናቸው። የስልክ መስመሩ እነዚህን ተሞክሮዎች እንዲመዘገቡ፣ እንዲታመኑ እና በባህል ብቁ በሆነ በአሰቃቂ ሁኔታ እንክብካቤ ምላሽ እንዲሰጣቸው የሚያስችል ቦታ ይፈጥራል።”
“የስልክ መስመሩ የጥላቻ ሰለባዎች በአካባቢያቸው ማህበረሰቦች ውስጥ ድጋፍ እንዳላቸው እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ እጠብቃለሁ” በማለት የHuman Rights Spokane የቦርድ አባል፣ Hershel Zellman ተናግረዋል። “እንዲሁም በስልክ መስመሩ የተሰበሰበው ስታቲስቲክስ በመጀመሪያ ደረጃ የጥላቻ ክስተትን ለመቅረፍ ትምህርታዊ ፕሮግራም እና የህግ አስፈጻሚ ስልቶችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ እንደሚውል እጠብቃለሁ።”
“ይህ የስልክ መስመር በባህል ብቁ የሆነ ድጋፍ እንደሚሰጥ፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እምነት እንደሚፈጥር እና ብዙ የማህበረሰብ አባላት ክስተቶች እንዲዘግቡ እንደሚያበረታታ ተስፋ እናደርጋለን” በማለት በዋሽንግተን ግዛት በሚገኘው Council on American-Islamic Relations የህግ ተሟጋች የሆኑት፣ Sabrene Odeh ተናግረዋል። “ስለ እስልምና ጥላቻ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር፣ የወደፊቱ ማህበረሰብ የሚያጋጥሙትን ፕሮግራሞች እና ተነሳሽነቶች ትክክለኛነት እንደሚያሻሽል እና ከማህበረሰቡ አባላት ጋር የሚስማማውን ድጋፍ እንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን። ይህንን የስልክ መስመር በማዘጋጀት ላይ የሙስሊም ማህበረሰቡን መወከል የሙስሊሞች ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጠው እና ዋጋ እንዳለው የሚያሳየውን መሌክት ያጠናክራል።”
“ድርጅታችን የምናገለግለው ማህበረሰብ ታማኝ መልዕክተኛ ነው” በማለት የዋሽንግተን West African Center የፕሮግራሞች ዳይሬክተር Momodou Jobe ተናግረዋል። “ድምጻችን ማህበረሰባችን ከሚነግረን ነገር የሚመጣ ሲሆን የስልክ መስመሩን በማዘጋጀት የሚኖረን ተሳትፎ የማህበረሰባችንን ድምጽ ወደ ክፍሉ ያመጣል።”
“በአይሁድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ብዙዎች እያደገ የመጣው ጸረ ሴማዊነት ከሚያስከትላቸው ውጤቶች ጋር እየተናነቁ ነው እና ተጨማሪ መርጃዎችን እና አገልግሎቶችን ይፈልጋሉ” በማለት በፓሲፊክ ሰሜን ምዕራብ Anti-Defamation League ክልላዊ ዳይሬክተር፣ Miri Cypers ተናግረዋል። “በK-12 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከመድሎ ክስተቶች ጋር ከሚታገሉ ወጣቶች ጀምሮ ዛቻ እስከሚያጋጥማቸው የማህበረሰብ ተቋማት ድረስ፣ የስልክ መስመሩ ለባህል ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ይሰጣል።”
“የሲክ ማህበረሰብ ለፍትህ እና ለሁሉም ሰው እኩልነት በጽናት ይቆማል” በማለት የKhalsa Gurmat Center ዋና ዳይሬክተር፣ Jasmit Singh ተናግረዋል። “የስልክ መስመር መጀመሩ ተጽዕኖ ወይም ጥላቻ የደረሰባቸው ሰዎች ድምጻቸው እንዲሰማ እና ክስተቶቹ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ወሳኝ ዘዴ በመሆኑ እናመሰግናለን። ይህ የስልክ መስመር ማህበረሰቦችን ያበረታታል እንዲሁም በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ለጥላቻ ቦታ እንደሌለ የሚገልትሰውን መልዕክት ያጠናክራል።”
የዋሽንግተን የጥላቻ ወንጀሎች እና የመድሎ ክስተቶች የስልክ መስመር በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት atg.wa.gov/report-hate ይጎብኙ።
ፍቺዎች
የዋሽንግተን ህግ የጥላቻ ወንጀልን እንደ የአንድን ሰው ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ የዘር ሀረግ፣ የትውልድ ቦታ፣ ጾታ፣ የፆታ ዝንባሌ፣ የፆታ መግለጫ ወይም ማንነት፣ ወይም አካል ጉዳተኝነት ላይ ተመስርቶ የሚሰነዘር ጥቃት፣ የንብረት ውድመት ወይም የአካል ጉዳት ወይም የንብረት ጉዳት የሚያደርሱ ማስፈራሪያዎች በማለት ይገልጸዋል።
የመድሎ ክስተቶች በተፈጥሮ ወንጀለኛ ያልሆኑ እና ሁከትን፣ ዛቻን እና የንብረት ውድመትን የማያካትቱ የጭፍን ጥላቻ ድርጊቶች ናቸው። የመድሎ ክስተቶች በወንጀል ባያስከስሡም ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
-30-
የዋሽንግተን ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዋሽንግተንን ህዝብ እና ግዛት ያገለግላል። የግዛቱ ትልቁ የህግ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፣ የAttorney General’s Office በዋሽንግተን ላሉ እያንዳንዱ የክልል ኤጀንሲ፣ ቦርድ እና ኮሚሽን የህግ ውክልና ይሰጣል። በተጨማሪም ጽህፈት ቤቱ የሸማቾች ጥበቃን፣ የሲቪል መብቶችን እና የአካባቢ ጥበቃ ህጎችን በማስከበር ህዝቡን በቀጥታ ያገለግላል። ጽህፈት ቤቱ በዋሽንግተን 39 አውራጃዎች ውስጥ በ38ቱ የሽማግሌዎችን ማጎሳቆል፣ ሜዲኬድ ማጭበርበርን ይከሳል እና የፆታዊ ጥቃት አዳኝ ጉዳዮችን ይቆጣጠራል። የበለጠ ለማወቅ www.atg.wa.gov ን ይጎብኙ።
የሚዲያ መገኛ አድራሻ፦
ኢሜይል፦ press@atg.wa.gov
ስልክ፦ (360) 753-2727
አጠቃላይ የመገኛ አድራሻዎች፦ እዚህ ጠቅ ያድርጉ (እንግሊዝኛ)
የሚዲያ መርጃ መመሪያ እና Attorney General’s Office በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች
Other Languages